የዲጂታል ትምህርት
የዲጂታል ትምህርት
ኢትዮጵያ ተማሪዎችና ወጣቶች በቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርትና ክህሎት እንዲያገኙ ለማስቻል የዲጂታል ስርዓት ትምህርትን በዋነኛነት እያስፋፋች ትገኛለች። የኢንተርኔት ትስስር መንገዶቸን በማመቻቸት እንዲሁም የዲጂታል መሣሪያዎችን እና የኢ-ለርኒንግ (E-learning) ግብዓቶችን በትምህርት ቤቶችና በስልጠና ማዕከላት ውስጥ በማካተት እነዚህ መርሃ ግብሮች የመማር ዕድሎችን ያሰፋሉ፤ የትምህርት ክፍተቶችን ይደፍናሉ፤ እንዲሁም ተማሪዎችን ለዘመናዊው የሥራ ዓለም ዝግጁ ያደርጋሉ። ዲጂታል ትምህርት ተማሪዎችን በቴክኖሎጂ፣ በችግር አፈታት እና በፈጠራ ረገድ አስፈላጊ የሆኑ ክህሎቶችን የሚያስታጥቅ ሲሆን፤ ይህም በትምህርታቸውና በሙያቸው ስኬታማ እንዲሆኑ እንዲሁም ለሐገሪቱ አጠቃላይ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትና ልማት የድርሻቸውን እንዲያበረክቱ ይረዳቸዋል።
ለተጨማሪ የመረጃ አማራጮች
https://linktr.ee/addisababacommunication