የእሳት ጢስ በአጋጣሚ አይንቀሳቀስም።

image description
- ሁነቶች fire disaster    0

የእሳት ጢስ በአጋጣሚ አይንቀሳቀስም።

🔥 የእሳት ጢስ በአጋጣሚ አይንቀሳቀስም።

#AAFDRMC_ጢስ ወደ እሳቱ እየተመለሰ ሲንቀሳቀስ ቢታይ፣ ይህ የግፊት (pressure)፣ ያልተመጣጠነ አየር መውጫ–መግቢያ (ventilation imbalance) እና የፍሎው መንገድ ቁጥጥር (flow-path control) እየሰራ መሆኑን የሚያሳይ ምልክት ነው። ጢስ በጣሪያ ስር ሲንከባለል የቦታው አቀራረብ (geometry) እና የጠንካራ መከላከያዎች — እንደ ግድግዳ — የጢስ ፍሰትን ወደ ውስጥ፣ ወደ እሳቱ መነሻ (seat of the fire) ሊመልሱት ይችላሉ፤ ከእሳቱ ርቆ እንዲሄድ ሳይሆን፣በዚህ ሁኔታ፣ የሚንከባለለው ጢስ በመግቢያ (intake) በኩል ነው እንጂ በመውጫ (exhaust) በኩል አይደለም። 

የመውጫ ክፍት ቦታ መጠን ከመግቢያው ጋር እኩል ወይም ከዚያ በላይ ሲሆን፣ ስርዓቱ ግፊትን ለማመጣጠን ይሞክራል። ውጤቱም? አየር በግፊት ወደ ውስጥ ይገባል — ጢስንም ከእሱ ጋር ወደ እሳቱ ይጎትታል።
የመግቢያና የመውጫ ክፍት ቦታዎች ሁልጊዜ የሚገባውንና የሚወጣውን አየር ለማመጣጠን እየሰሩ ናቸው። ጋዞች ከሚገባው አየር በፍጥነት ሲወጡ፣ የመግቢያ በኩል ንቁ (active) ይሆናል፣ እና የጢስ እንቅስቃሴም ያንን ያልተመጣጠነ ሁኔታ ያሳያል።ይህ አንድ-አቅጣጫ የፍሰት መንገድ (unidirectional flow path) ነው — እና ፋየርፋይተሮች ሁኔታዎችን ሲያነቡ እጅግ አስፈላጊ ምልክት ነው።

🔥 ቀድሞ አንብቡት።
💧 ቀድሞ አቀዝቅዙት።
🌬 አየርን ቁጥጥር ውስጥ አድርጉ።

#AAFDRMC