ኮሚሽኑ የአንድ ወር እቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ::

image description
- ሁነቶች ጨረታ ስለመከፈት…    0

ኮሚሽኑ የአንድ ወር እቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ::

ኮሚሽኑ የአንድ ወር እቅድ አፈጻጸሙን ገመገመ:: 

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የጥቅምት ወር 2018 ዓ.ም እቅድም አፈጻጸምን አስመልክቶ የማዕከል ከፍተኛ አመራሮችና የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ አስኪያጆች በተገኙበት ዛሬ ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ተገምግሟል ።

በግምገማ መድረኩ በሁሉም ዘርፎች በወሩ በማዕክልና በቅርንጫፍ ጽ/ቤት ስራ ኃላፊዎች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት የተካሄደበት ሲሆን የተከናወኑ ስራዎችም እቅድን መሠረት ያደረጉ ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን በግምገማው የተገለጸ ሲሆን በሪፖርቱ መነሻነትም በተለይም ሰብዓዊ ድጋፍ በራስ አቅም የመሸፈን ስራን አስመልክቶ የተከናወኑ ተግባራትና ውስንነቶች ላይ ትኩረት ተሰጥቶት ውይይት ተካሂዶበታል ።

የግምገማ መድረኩን የመሩት ም/ኮሚሸርና የአደጋ ቅነሳ ዘርፍ ኃላፊ የዋና ኮሚሸነር ተወካይ 

ደሳለኝ ፉፋ እንደተናገሩት በጥቅምት ወር የተ ከናወኑ ስራዎች አበረታች መሆናቸውን ጠቅሰው በተለይም በሀገር አቀፍና በከተማ ደረጃ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት የተጀመረ ተግባር ቢሆንም አንዳንድ ባለድርሻ አካላት የሚጠበቅባቸው ኃላፊነት እየተወጡ ባለመሆኑ በአፈጸጸም ዙሪያ ውስንነት ከታየባቸው ባለድርሻ አካላት ጋር መወያየት እንደሚገባ ተናግረዋል:: 

በመድረኩ ማጠቃለያ በቀጣይ ወራት የሚከናውኑ ተግባራት ላይ የትኩረት አቅጣጫ ተቀምጧል።

ለእሳትና ሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!