ከመጭው የህዳር ወር ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ...

image description
- ሁነቶች fire disaster    0

ከመጭው የህዳር ወር ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ሊመዘገብ ይችላል

ከመጭው የህዳር ወር ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ሊመዘገብ ይችላል

AMN - ጥቅምት 12/2018 ዓ. ም

ከመጭው የህዳር ወር ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ የቀኑ ዝቅተኛ የሙቀት መጠን ሊመዘገብ እንደሚችል የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

አዲስ አበባ ከተማን ጨምሮ በምስራቅ አማራ እና በምስራቅ ኦሮሚያ አካባቢዎች ከመጭው ህዳር ወር ጀምሮ ከ10 ዲግሪ ሴልሺየስ በታች የሆነ ሙቀትን ሊያስተናግዱ እንደሚችሉ በኢንስቲቲዩቱ የትንበያ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አሳምነው ተሾመ (ዶ/ር) ለኤ ኤም ኤን ተናግረዋል፡፡

በዚሁ ወቅት በከተማዋ አልፎ አልፎ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሊከሰት እንደሚችልም ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አንስተዋል፡፡

አሳምነው (ዶ/ር) አክለውም፣ ከሳይቤሪያ በመነሳት ወደ ኢትዮጵያ የሚነፍሰው ደረቅ እና ቀዝቃዛማ የአየር ሁኔታ የሚጠናከር በመሆኑ በተለይም ከህዳር ወር መጀመሪያ ሳምንት ጀምሮ ከእለት ወደ እለት የተለያየ መጠን ያለው ቅዝቃዜ ሊከሰት ይችላል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

በቅዝቃዜው ሊከሰቱ የሚችሉ የጤና እክሎችን ለመከላከል ያስችል ዘንድም ማህበረሰቡ ከወዲሁ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

በአጠቃላይ ከተማዋ የበጋውን ወራት ደረቅ ጸሀያማ እና ነፋሻማ የአየር ሁኔታን እንደምታስተናግድ ጠቁመዋል፡፡

በሌላ በኩል በሚቀጥሉት የበጋ ወራት ለአብዛኞቹ የደቡብ አጋማሽ የሀገሪቱ አካባቢዎች ሁለተኛ የዝናብ ወቅት እንደሚሆንም ዋና ዳይሬክተሩ አንስተዋል፡፡

በአይናለም አባይነህ