
የጉለሌ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በስነምግባርና መልካም አስተዳደር ዙሪያ ለሰራተኞች ስልጠና ሰጠ ።
የጉለሌ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በስነምግባርና መልካም አስተዳደር ዙሪያ ለሰራተኞች ስልጠና ሰጠ ።
ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም
በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ጉለሌ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ክፍል አዘጋጅነት ለቅርንጫፉ ጠቅላላ ሰራተኞች በስነ ምግባርና መልካም አስተዳደር ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጥቷል።
የስነምግባርና ፀረ ሙስና መከታተያ ባለሙያ አቶ ከፍያለው ዳባ የዚህ ስልጠና ዓላማ ቅርንጫፍ ፅህፈትቤቱ ሙስናን መከላከል ግንባር ቀደም ተግባር
በማድረግ ሰራተኞች የስነ ምግባር መርሆዎችን አውቀው ሙስናን ለመከላከል ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር ፅንሰ ሀሳቡ እንዲረዱ ማድረግ መሆኑን ገልፀዋል።
በስልጠናው ማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ሂሩት ሽፈራው ወደ ተቋማዊ አስተስተሳሰብ በመምጣት በቅርንጫፋ የሚታዩ የመልካም አስተዳደርና ብልሹ አሰራሮችን መታገልና ስራዎች በሚሰሩበት ጊዜ የሰራተኛው ሚና ምን እንደነበር መገምገም እንደሚገባና ቅሬታዎችን ለመፍታትና የስራ አካባቢው ላይ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን የስራ መገምገሚያ መድረክ በማዘጋጀት የነበረውን ክፍተት መድፈንና ሁሉም የስራ ክፍል የመልካም አስተዳደር ዕቅድ በማቀድ ስራዎችን በትጋት መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል ።
የአስተዳደርና መልካም አስተዳደር ፅንሰ ሀሳብ፤ የመልካም አስተዳደር መሰረታዊ መርሆዎች፤ የመልካም አስተዳደር አስፈላጊነት፤ የመልካም አስተዳደር ተግዳሮቶች እና መልካም አስተዳደርን መገንባት የሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች የስልጠናው አካል ናቸው።