አደጋን አስቀድሞ ለመከላከል የሚስችሉና ከኮሚሽኑ እየተላለፉ የሚገኙ የጥንቃቄ መልዕክቶችን መተግበር እንደሚገባ ተገለጸ።
አደጋን አስቀድሞ ለመከላከል የሚስችሉና ከኮሚሽኑ እየተላለፉ የሚገኙ የጥንቃቄ መልዕክቶችን መተግበር እንደሚገባ ተገለጸ።
በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ቅነሳ ዘርፍ በከተማው ከሚገኙ የክፍለ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት
በተገኙበት ትኩርቱን በአደጋ ቅነሳ ላይ ያደረገ ውይይት ዛሬ ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ.ም አካሂዷል ።
በመድረኩ ለውይይት መነሻ የሚሆን በከተማ በጥናት የተለዩ የአደጋ ዓይነቶችና ባለፉት10 ዓመታት በአዲስ አበባና አካባቢ ው ያጋጠሙ አደጋዎችና ያስከተሉት ጉዳት ዝርዝር የጥናት ሰነድ ቀረቦ ውይይት ተካሂዷል ።
የውይይቱ ተሳታሪዎች በቀረበው ሰነድ መነሻነት በሰጡት አስተያየት በአካባቢያቸው ለአደጋ ተጋላጭ ተብለው የተለዩ የስጋት ቦታዎች ላይ የማቅለያ እርምጃዎች እንዲወሰዱ እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰው የህብረተሰቡን የጥንቃቄ ባህል ለማሳደግ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች ላይ ከኮሚሽኑ ጋር በቅርበትና በትብብር እየሰሩ እንደሆነም አብራርተዋል ::
የውይይት መድረኩን የመሩት ም/ ኮሚሽነርና የአደጋ ቅነሳ ዘርፍ ኃላፊ ደሳለኝ ፉፋ እንደተናገሩት በከተማው ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ ቦታዎችን በጥናት በመለየት ከባለድርሻ አካላት ጋር
በመተባበር ለስጋቶቹ መፍትሄ እንዲያገኙ የማድረግ ተግባራትን እያከናወኑ መሆኑን ጠቅሰው ህብረተሰቡ ለአደጋ የሚያጋልጡ
አሠራሮችን ተረድቶ እራሱን ከአደጋ እንዲጠብቅ በተለያዩ ሚዲያዎችና በአደጋ ቅነሳ ባለሞያዎች የግንዛቤ ማስበጫ ተግባራትን በልዩ ትኩረት እየተከናውነ መሆኑን አብራተዋል ።
የአደጋ ስጋት ጥናትና ትግበራ ዳይሬክተር አቶ ዴሳሳ ጦና በበኩላቸው እንደተናገሩት በከተማችን እያጋጠሙ ያሉ አደጋዎች አብዛኛዎቹ በጥንቃቄ ጉድለት የሚከሰቱ በመሆኑ ህብረተሰቡ ከኮሚሽን መ/ቤቱ የሚተላለፉ የጥንቃቄ መልዕክቶችን በመተግበር እራሱን ከአደጋ እንዲጠብቅ አሳስበዋል ።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነው ያሳወቁ!