
"ከጂኦ ስትራቴጂያዊ ኩስመና ወደ ታደሠ ቁመና "በሚል ርዕሰ በተ ዘጋጀ ሰነድ ላይ ውይይት አካሂደዋል።
"ከጂኦ ስትራቴጂያዊ ኩስመና ወደ ታደሠ ቁመና "በሚል ርዕሰ በተ ዘጋጀ ሰነድ ላይ ውይይት አካሂደዋል።
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የማዕከል አመራር
ሠራተኞች "ከጂኦ ስትራቴጂያዊ ኩስመና ወደ ታደሠ ቁመና "በሚል ርዕሰ በተዘጋጀ ሰነድ
ላይ ዛሬ መስከረም 27 ቀን 2018 ዓ.ም ውይይት አካሂደዋል ።
የውይይት መድረኩን የመሩት የኮሚሽኑ ኮሚሸነር አህመድ መሀመድ እንደተናገሩት
የጂኦ ስትራቴጂ ሉአላዊነታችንን በአለማስከበራችን ምክንያት ከአጋጠመን ኩስመና መውጣት እንደሚገባን አስታወሰው በሴራና ኃላፊነት በጎደለው ሁኔታ እንድናጣ የተደረገው የባህር በር ጥያቄያችንን ዕውን በማድረግ የተጀመረውን ኢትዮጵያን ከፍታ ማስቀጠል ይኖርብናል ብለዋል።
የኮሚሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ መልአኬ አለማየሁ በበኩላቸው እንደተናገሩት ለረጅም ጊዜ የማይነኩ ሆነው የቆዩ አጀንዳዎችን ኢትዮጵያ ማንሳቷ ዓለም አቀፍ አጀንዳ እየሆነ መምጣቱ ጠቅሰው በተለይም ባልተገባ መንገድ ያጣነውን የባህር ጥያቄ ሰላማዊ መንገድ መሠረት በማድረግ ሌሎች አማራጮችም በመጠቀም የወደብ ተጠቃሚነታችን ማረጋገጥ ይገባናል ብለዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎችም በሠጡት አስተያየትም ሀገራችን ኢትዮጵያ በቅርቡ የተጠናቀቀው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ ሌሎች ሠፋፊ ፕሮጀክቶችን ጀምራ ወደ ተግባር የገባች ታላቅ ሀገር ብትሆንም የውስጥና የውጭ ባንዳና
ባዳዎች ዕድቷን ለመጎተት አፍራሽ ተልዕኮ ላይ መሰማራታቸውን ገልጸው
"ከጂኦ ስትራቴጂያዊ ኩስመና ወደ ታደሠ ቁመና ለመሸጋገር የተጀመረውን ጥረት በማገዝ ኃላፊነታቸውን እንደሚወጡ አረጋግጠዋል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገ ተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነው ያሳውቁ !