የሆረ ፊንፊኔ ኢሬቻ በዓል ከማናቸውም አደጋ ተጠብቆ እንዲያልፍ በቂ ዝግጅት ተደርጓል::
የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የሆረ ፈንፊኔ ኢሬቻ በዓል ከአደጋ ክስተት ተጠብቆ እንዲከበር አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ ወደስራ መገባቱን የኮሚሽኑ ኮሚሽነር አህመድ መሀመድ አስታውቀዋል።
ኮሚሽኑ በአደጋ ቅነሳ ዘርፉ በተለየዩ አማራጮች የጥንቃቄ መልዕክቶችን ሲያስተላልፍ መቆየቱን የጠቀሱት ኮሚሽነሩ በዓሉ በሚከበርበት ቦታም ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ጋር የተቀናጀ የቅድመ ሆስፒታልና የአንቡላንስ አገልግሎትን እንዲሁም የአደጋ ምላሽ ዘርፉ በዓሉ በሚከበርበት ቦታ በተለያዩ አቅጣጫዎች አስፈላጊውን ጥበቃ በማድረግ ላይ እንደሆኑ ኮሚሽነር አህመድ ገልጸዋል::
በሌላ በኩልም በማናቸውም ስፍራ ለሚያጋጥሙ አደጋዎች ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል በአስራ አንዱም ቅርንጫፍ ጽ/ቤት እና በማዕከል በቂ ዝግጅት እንደተደረገም ኮሚሽነሩ አስታውቀዋል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንተገኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነው ያሳውቁ !