
በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን 11ኛ ቅርንጫፍ የሆነው የካ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
በእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን 11ኛ ቅርንጫፍ የሆነው የካ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን 11ኛ ቅርንጫፍ የሆነው የካ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት የከተማ እና የክፍለ ከተማ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ዛሬ መስከረም 13 ቀን 2018 ዓ.ም ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።
በምርቃት መርሀ ግብሩ ላይ መልእክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አህመድ መሀመድ እንደገለፁት ኮሚሽኑ በየትኛውም ቦታ በማንኛውም ሰአት የሰውን ህይወት እና ንብረት ለማዳን ለሊት ከቀን መስዋእትነት እስከመክፈል እየሰራ እንደሚገኝ አንስተው ዛሬ ክፍት የተደረገው ለከተማዋ 11ኛ ቅርንጫፍ የሆነው የካ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ለህብረተሰቡ ይበልጥ ቅርብ እና ተደራሽ ለመሆን እንጂ ስራውን ሲሰራ መቆየቱን ገልፀው ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ እንዲከፈት ለአገዙ አካላት ምስጋና አቅርበዋል።
የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ኃይሌ በበኩላቸው ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ በተለያዩ ምቹ ባልሆኑ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ በክፍለ ከተማው እሳትና ጎርፍ አደጋ ሲያጋጥም ፈጣን ምላሽ ሲሰጥ መቆየቱን አንስተው ለህብረተሰቡ ይበልጥ ተደራሽ ሆኖ አገልግሎቱን እንዲሰጥ አስቻይ ሁኔታ መፈጠሩን ገልፀው በቀጣይም የራሱን ህንፃ ገንብቶ ይበልጥ የተጠናከረ አገልግሎት እንዲሰጥ ሁሉም ሊያግዝ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ኒቆዲሞስ ቡቹ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ በ2016 ነሃሴ 21 መቋቋሙን አንስተው የተመደቡ ሰራተኞች በቦታ እጥረት ምክንያት ተበታትነው ሲሰሩ እንደነበር በማንሳት ኮሙሽኑ ከየካ ክፍለ ከተማ ጋር በመተባበር ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቱ የራሱ ቢሮ እና ማቴሪያል ተሟልቶለት የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጥ በማስቻላቸው ምስጋና አቅርበው በቀጣይም የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ተቋሙ እንጀሚሰራ ገልፀዋል።
በመርሃ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አህመድ መሀመድ፣የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፍፁም ኃይሌ፣የየካ ክፍለ ከተማ የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ ማስተባበሪያ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መገርሳ ገላናን ጨምሮ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን ተቋሙ በተሟላ መልኩ ለአገልግሎት ክፍት እንዲሆን ላገዙ አካላት እውቅና ተሰጥቷል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነው ያሳውቁ!