የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት ያለምንም አ...

image description
- ሁነቶች training    0

የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት ያለምንም አደጋ ክስተት ተከብረው እንዲጠናቀቁ አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ ።

እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አመራርና ሠራተኞች የመስቀል ደመራና የኤሬቻ በዓላት ከማናቸውም አደጋ ተጠብቀው ለማክበር በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ዛሬ መስከረም ቀን 2018 ዓ.ም ውይይት አካሂደዋል።

የውይይት መድረኩን የመሩት የኮሚሽኑ ኮሚሸነር አህመድ መሀመድ እንደተናገሩት በዓላቱ የአደባባይ በዓላት በመሆናቸው በርካታ እንግዶችና የከተማው ነዋሪዎች የሚሳተፉበት በመሆኑ ሁለቱም በዓላት ያለምንም አደጋ ክስተት ተከብረው እንዲጠናቀቁ በተለይም በአደጋ ቅነሳና በአደጋ ምላሽ ዘርፍ በቂ ዝግጅት ተደርጎ ወደስራ መገባቱን አስታውቀው በኮሚሽኑ በሁሉም ዘርፎች የሚገኙ አመራርና ሠራተኞች በሚሰጣቸው ስምሪት መሠረት ኃላፊነታቸው እንዲወጡ አሳስበዋል ።

ም/ኮሚሽነርና የአደጋ ቅነሳ ዘርፍ ኃላፊ ደሳለኝ ፉፋ በበኩላቸው እንደተናገሩት በዓላቱን ታሳቢ ያደረገ ዕቅድ ተዘጋጅቶ ወደስራ መገባቱን ጠቅሰው በሁሉም ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የሚገኙ የአደጋ ቅነሳ አመራርና ባለሞያዎች በተመረጡ ቦታዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እያከናወኑ መሆናቸውንና በተለያዩ የሚዲያ አግባቦች የጥንቃቄ መልዕክቶችም እየተላለፉ መሆኑን አብራርተዋል።

በሌላ በኩልም የአደጋ ምላሽ ዘርፉ በዓላቱ በሚከበሩባቸው ቦታዎች ላይ አስፈለጊው ጥበቃ እንደሚደረግና ለዚህም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ም/ኮሚሽነርና የአደጋ ምላሽ ዘርፍ ኃላፊ ኮማንደር መስፍን አያሌው ተናግረዋል ።

በውይይት መድረኩ "በእመርታና ማንሰራራት የታጀበ ህዝባዊ በዓላትን በጋራ እናክብር " በሚል መሪ ቃል የመስቀል ደመራና የኢሬቻ በዓል አከባበርን አስመልክቶ የተዘጋጀ ሰነድ በኮሚሸኑ ጽ/ቤት ኃላፊ በወ/ሮ መልአኬ አለማየሁ የቀረበ ሲሆን

በገለጻቸውም የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ በዓላት ከሀገራችን አልፎ በአፍሪካ እንዲሁም በአለም አቀፍ ደረጃ በቅርስነት የተመዘገቡ እና የዓለም ህዝብ እሴት የሆኑ በዓላት መሆናቸው ገልጸዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው እንደተናገሩት ለበዓላቱ ስኬታማነት እንደኮሚሽን መ/ቤቱ ሠራተኛና እንደከተማ ነዋሪ የበኩላቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ አረጋግጠዋል ።