የሸገር ከተማ አስተዳደር ለኮሚሽን መ/ቤቱ እዉ...

image description
- ሁነቶች fire disaster    0

የሸገር ከተማ አስተዳደር ለኮሚሽን መ/ቤቱ እዉቅና ሰጠ።

የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር በአደጋ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፍ ለሸገር ከተሞች ላበረከተዉ አስተዋጾኦ ዛሬ ግንቦት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከአስተዳደሩ እዉቅና ተሰጥቶታል።

ለኮሚሽን መ/ቤቱ ዕዉቅና የተሰጠዉ በዛሬዉ ዕለት በሸገር ከተማ አስተዳደር የመልካ ናኖ ክፍለ-ከተማ የአደጋ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከሉን ባስመረቀበት ስነ-ስርዓት ላይ ነዉ።

በመርሀ ግብሩ ላይ የሸገር ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ዶ/ር ተሾመ አዱኛ እንደተናገሩት የሸገር ከተማ አስተዳደር በክፍለ-ከተሞቹ ሊያጋጥሙ የሚችሉ አደጋዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲቻል ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ሲሰራ መቆየቱን ጠቅሰዉ የሸገር ከተማ አስተዳደርና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ባደረጉት ጥረት የእሳት አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል መቋቋሙን አብራርተዋል።

ዶ/ር ተሾመ አያይዘዉም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በሸገር ከተማ አስተዳደር የተለያዩ አደጋዎች በአጋጠሙ ጊዜ ፈጣን ምላሽ በመስጠት እንደዚሁም ዛሬ ለምረቃ የበቃዉ ማዕከል ዕዉን እንዲሆን የሙያና የቴክኒክ ድጋፍ በመስጠት ላበረከተዉ አስተዋጾኦ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል።

የመልካ ናኖ ክፍለ-ከተማ

ስምንት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና አምስት አምቡላንሶች አሟልቶ የማዕከሉን ህንጻ አስመርቋል።

በማዕከሉ የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ በኮሚሽኑ የማዕከልና የማሰልጠኛ ማዕከል እንደዚሁም የሁሉም ቅርንጫፍ ጣቢያ አመራሮች በክብር እንግድነት ተገኝተዋል።

ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!