
የጎርፍ አደጋን አስቀድሞ ለመከላከል በሚያስችለዉ የጽዳት ንቅናቄ ስራ ላይ የኮሚሽኑ ባለሞያዎች መሳተፋቸዉ ተገለጸ።
የጎርፍ አደጋን አስቀድሞ
ለመከላከል በሚያስችለዉ የጽዳት ንቅናቄ ስራ ላይ የኮሚሽኑ ባለሞያዎች መሳተፋቸዉ ተገለጸ።
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 9 ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት አስተባባሪነት ዛሬ ግንቦት 2 ቀን 2017 ዓ.ም በተካሄደዉ የፅዳት ንቅናቄ ላይ በኮሚሽኑ የአቃቂ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራርና ባለሞያዎች ተሳትፈዋል።
የጽዳት ንቅናቄዉ ስራ የከተማዋን በጎ ገጽታ ከማስቀጠሉም ባሻገር መጪዉ የክረምት ጊዜን ተከትሎ በፍሳሽ መስመሮች መዘጋጋት ምክንያት ሊፈጠር የሚችለዉን የጎርፍ አደጋ አስቀድሞ ለመከላከል የሚያስችል እንደሆነ ተገልጿል።
በጽዳት ንቅናቄዉ መርሀ ግብር ላይም ህብረተሰቡ ለአደጋ የሚያጋልጡ አሰራሮችን ተረድቶ እራሱንና አካባቢዉን ከአደጋ ለመከላከል እንዲችል በመርሀ ግብሩ ላይ ለተገኙ ተሳታፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የአደጋ ምላሽ ባለሞያዎች ተሰጥቷል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!