የከተማዉ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ለኮሚሽኑ መካከለኛ አመራርና ባለሞያዎች የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት ጀመረ ።

የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ከእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከልዩ ልዩ የሰራ ክፍሎች ለተዉጣጡ መካከለኛ አመራሮችና ባለሞያዎች ለሶስት ቀናት የሚቆይ በስሜት ልህቀት ፣ በሙያዊ ስነምግባር ፣ በተግባቦትና በቅንጅታዊ አሰራር ላይ ያተኮረ ለአሰልጠኞች አቅም ግንባታ ስልጠና ዛሬ ሚያዚያ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ተጀምሯል።
በስልጠናዉ መክፈቻ መርሀ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት በኮሚሽኑ የድህረ አደጋና መልሶ ማቋቋም ዘርፍ ኃላፊ ም/ኮሚሽነር ጥላሁን ቶላ እንደተናገሩት ኮሚሽን መ/ቤቱ የሚሰጠዉን አገልግሎቶች ለማሻሻል የሚያስችል የአሰልጠኞች ስልጠና አዘጋጅቶ ስልጠናዉ እየሰጠ ላለዉ የከተማዉ ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ምስጋናቸዉን አቅርበዉ የሚሰጠዉ ስልጠና መካከለኛ አመራሩና ባለሞያዎች ያሉባቸዉን የአቅምና የክህሎት ዉስንነቶች እንደሚያሻሻል ተናግረዋል።
የስራ አስኪያጅ ጽ /ቤት አማካሪ አቶ ይብሬ እስማኤል በበኩላቸዉ እንደተናገሩት የስራ አስኪያጅ ጽ/ቤቱ በስሩ ያሉ የተጠሪ ተቋማትን የስልጠና ፍላጎት መሰረት ያደረጉ ልዩ ልዩ ስልጠናዎችን አዘጋጅቶ እየሰጠ መሆኑን ጠቅሰዉ በዛሬዉ ዕለት የሚጀመረዉ ስልጠና የዚሁ አካል በመሆኑ ሰልጣኞች ከስልጠናዉ በቂ እዉቀትና መረጃ እንደሚያገኙም ገልጸዋል።
ለእሳትና ለሌሎች ድንገተኛ አደጋዎች እንዲደሁም ለአንቡላንስ አገልግሎቶች በ939 ፈጥነዉ ያሳዉቁ!